News & Articles

News50ኛ አመት የአጋርነት በዓል
  • 50ኛ አመት የአጋርነት በዓል

    ኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን(ልማአኮ) ከአጋሩ የኪንደርኖትሂልፌ (KNH) መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ተቋም ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የኢትዮጲያ አካባቢዎች የተሰሩ የልማት ስራዎችን የሚዘክር 50ኛ አመት የአጋርነት በዓል በማክበር ላይ ይገኛል።

    አጋር ተቋሙ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በልጆች እና ወጣቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን ባለፉት 50 አመታት (1966 - 2016) ከቤተክርስቲያኒቱ ልማት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ልጆችና ወጣቶች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ውጤታማና ምርታማ ዜጎች መሆን ይችሉ ዘንድ ዘርፈብዙ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የትምህርት እድሎችን እና የሙያ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።

    በዓሉም በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች እና በኤግዚቢሽን በዛሬው እለት በመከበር ላይ ይገኛል። በመክፈቻ መርሀግብሩም ላይ የጀርመን አምባሳደር በኢትዮጵያ፣ የኪንደርኖትሄልፌ ተጠሪ፣ የድርጅቱ የ50 ዓመታት አጋር ከሆኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን እንዲሁም የቤተክርስቲያናቱ የልማት ተቋማት አመራሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ አስራ ሦስት አጋር ድርጅቶች፣ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

    - - - - -

    +3


LET'S START DOING YOUR BIT FOR THE WORLD. JOIN US AS A VOLUNTEER.
Commited to creating a caring, just & prosperous society

CONTACT

Address

Addis Ababa, Arada Subcity Woreda 6 House Number 922

Tel +251 111-574-630

P.O.Box 81065

© 2022 EECMY DASSC. All Rights Reserved.

Powered by M.A.D Technologies & Green Tech